[የጋራ መግለጫ] በኢምግሬሽን ደንብ ማሻሻያ አንቀጵ 63 ንሁስ አንቀጵ 1 ላይ ውይይት እንዲደረግ የሚያሳስብ ጋዜጣዊ መግለጫ

ማስታወቂያ የተሻሻለ

한국어 / English / français / العربية / فارسی / русский

[የጋራ መግለጫ] በኢምግሬሽን ደንብ ማሻሻያ አንቀጵ 63 ንሁስ አንቀጵ 1 ላይ ውይይት እንዲደረግ የሚያሳስብ ጋዜጣዊ መግለጫ

የጋዜጣዊ መግለጫ ቀን መስከረም 26 ቀን 2023 ዓ.ም (ማክሰኞ)

በኢምግሬሽን ደንብ ማሻሻያ ላይ ምክረ ሃሳብ ፡ በኮሪያ ብሄራዊ ምክር ቤት እና የሲቪል ማህበረሰብ አጋሮች የቀረበ ጋዜጣዊ መግለጫ

ከአራት ዓመት በላይ የታሰረ ስደተኛ ፡ ከግርፋት ያልተናነሰ በደል የደረሰበት ጥገኝነት አመልካች እግሩና እጁ ከአካሉ ጋር ወደኋላ ተጠፍንጎ (እዚህ ሀገር እንደ ሽሪምፕ ፖስቸር ተብሎ የሚታወቀው አይነት) እንዲሁም ለብቻው ታስሮ ፡ ትንሽ ልጅ ከአዋቂ ወንዶች ጋር በአንድ ክፍል ውስጥ ታስሮ

እነዚህ በሙሉ የታሰሩት በአንድ ደንብ ምክንያት ነው፡ አንድ ከኮሪያ ሀገር እንዲባረር የተወሰነበትን ሰው በፓስፖርት አለመኖር ወይም ትራንስፖርት አለመመቻቸት ምክንያት ወይም በሌላ ያልታወቀ ምክንያት መሄድ የማይችል ሆኖ ሲገኝ የአካባቢው የኢምግሬሽን የበላይ ሃላፊ በማቆያ ቤት ከሀገር ተባሮ መሄድ እስኪችል ወይም እስክትችል ድረስ ሊያስር ስለሚችል ነው፡፡ ይሄም የሚሆነው በኢምግሬሽን ደንብ ማሻሻያ አንቀጵ 63 መሰረት በአስቸኳይ የማይባረር ሰው “ላልተወሰነ ጊዜ” አንዲታሰር ስለሚፈቅድ ነው፡፡

ማሰር አስፈላጊ ስለመሆኑ ምንም አይነት ግምገማ ወይም ውሳኔ አይጠይቅም፡ በተጨማሪ ከሀገር እንዲባረር የተወሰነበትን ሰው ምን ያህል ጊዜ አስሮ ማቆየት ይቻላል የሚለው ለአካባቢው የአስተዳደር ቢሮ የተተወ ነው፡፡ በተግባር ግን የማሰር ትዕዛዝ የሚወጣው ከሀገር የማባረር ውሳኔ እንደተላለፈ ወዲያውኑ ነዉ::

በማቆያ ጣቢያ ማሰር የሚያስከትለውን ጉዳት ለመገንዘብ የሚያስችል ውሳኔ ላይ ለመድረስ : ለማነፃፀር እና ለመወሰን የሚያስችል ሁኔታ አይጠይቅም:: ለምሳሌ አንድ ከሀገር ተባራሪ ሲታሰር ግለሰቡ ከበሽታ ነፃ ስለመሆኑ ወይም ግለሰቧ ያረገዘች እንደሆነ ወይም በኮሪያ ውስጥ የቤተሰብ ሃላፊ መሆናቸውን: ወይም የስደተኝነት ማመልከቻው ሂደት የሚወስደው ጊዜ መራዘም ወይም የመብት ጥሰቶች መፍትሄ ስለማግኘታቸው ግምት ውስጥ አይገባም::

በዚህም ውጤት መሰረት ስደተኞች ላይ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቅሬታ የሚያስነሱ ሆነው ተገኝተዋል: እንደ ምሳሌም ወደ ሀገራቸው መመለስ የማይችሉ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና በስራ ወቅት የተራዘመ ደሞዝ አለመከፈል ሂደት ምክንያት ታሳሪዎች ያለ ጥፋታቸው ራሳቸውን የተራዘመ የእስር ጊዜ ውስጥ ያገኙታል::

ተቀባይነት ያለው ቢመስልም እንኳን አካላዊ የመንቀሳቀስ ነፃነት ማጣት የሰውን ክብር የሚጥስበት ገደብ ተሻግሯል:: ስለሆነም ምንም አይነት ዓላማ ቢኖረውም የማቆያ እስርን ማስፈፀም ወደ አስፈላጊው ዝቅተኛ ጊዜ መውረድ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም በተገቢው ሁኔታ መሰረት በጥብቅ መመዘኛዎች እና ሂደት መከናወን ይገባዋል:: በተለይ ገደብ የሌለው እስር በምንም ዓይነት ሁኔታና መመዘኛ ተቀባይነት የሚያገኝ መሆን የለበትም::

እኤአ በ2015 የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ (UN Human Rights Committee (UNHRC) ለደቡብ ኮሪያ መንግስት የኢምግሬሽን እስር ጊዜ የተወሰነ እንዲሆን እና ማሰር የመጨረሻው አማራጭ ብቻ ካልሆነ በስተቀር እንዳይፈፀም ምክረ ሃሳብ አቅርቦ ነበር:: እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የፀረ ዘር ተኮር ጭቆና ኮሚቴ (UN Committee on the Elimination of Racial Discrimination (UNCERD) እኤአ በ 2019 ጥገኝነት ጠያቂዎችን የማሰር ህጋዊ ተገቢነቱን በመደበኛነት ነፃ በሆነ መንገድ መገምገም እንዳለበት እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ማሰር የመጨረሻው አማራጭ ብቻ ካልሆነ በስተቀር እንዳይፈፀም: እንዲሁም ለአጭር ጊዜ ብቻ የሚፈፀም እንዲሆን: ስደተኞች ታስረው የሚቆዩበት ጊዜ የታወቀ ሆኖ እንዲመሰረት: ከማሰር ይልቅ ሌሎች የአማራጭ እርምጃዎች ቅድሚያ እንዲሰጣቸው እና ልጆች እና ዝቅተኛ የማህበረሰብ ክፍል አባላት ፈፅሞ እንዳይታሰሩ ሲል ምክረ ሃሳብ አቅርቦ ነበር:: ልጅ ማሰር እንዲቆም የተደረገው ቅስቀሳ በሰፊው ትኩረት አግኝቶ ነበር:: እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት የልጅ መብቶች ኮሚቴ (UN Committee on the Rights of the Child (UNCRC) በምንም የኢምግሬሽን ተያያዥ ጉዳዮች አመካኝቶ ልጆችን ማሰር ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ ገልፆ ፈፅሞ በፍጥነት እንዲቆም ሲል አሳስቧል፡፡

በዓለም ዙሪያ ሀገራት የእስር ጊዜን በመወሰን ረገድ ጥብቅ መርህን የሚከተሉ ሲሆን በተጨማሪም በነፃ እና ገለልተኛ አካል የኢምግሬሽን እስርን በተመለከተ ግምገማ እንዲካሄድ ያደርጋሉ::በአውሮፖ ዩኒየን የተመላሽ ጉዳይ ዳይሬክቲቭ መሰረት አባል ሀገራቱ የኢምግሬሽን እስርን በተመለከተ የጊዜ ገደብ የተቀመጠ ሲሆን የመነሻ እስር ጊዜ 6 ወራት ሆኖ እስከ 12 ወራት ድረስ ብቻ ይቆያል:: ይህም ሆኖ ፈረንሳይ ከፍተኛውን የእስር ጊዜ ለ90 ቀናት ብቻ የገደበች ሲሆን: በታይዋን ሀገርም ለ 100 ቀናት የተገደበ ሲሆን : በደቡብ አፍሪካም የእስር ጊዜ ለ 120 ቀናት ብቻ ሆኗል::

የኮሪያ ህገመንግስታዊ ችሎት ሶስት ጊዜ የኢምግሬሽን እስር “ህገመንግስታዊ አይደለም” ብሎ የመወሰን እድሎች የነበሩት ቢሆንም በኢምግሬሽን ደንብ አንቀፅ 63 መሰረት እስር በጣም በቀላሉ እና አሻሚ በሆነ መንገድ እየተፈፀመ ይገኛል:: በሁለተኛው “ በማቆያ ማሰር ህገመንግስታዊ አይደለም” ተብሎ በቀረበው አቤቱታ ወቅት በአብላጫው ተሰሚነት ያገኘ እና ህገመንግስታዊ እንዳልሆነ የታመነበት ቢሆንም በፍርድ ሂደቱ ወቅት የስድስት ሰው ኮረም መሙላት ሳይችል በመቅረቱ ህገመንግስታዊ ነው የሚል ውሳኔ በመተላለፉ ምክንያት ኳሱ ወደ ብሄራዊ ፖርላማ በድጋሚ ተመልሷል:: ሆኖም ህግ አውጪው አካል እጁ ላይ ያስቀመጠው ቢሆንም በስዎን ዲስትሪክት ችሎት ጥየቃ መሠረት ጉዳዪ ወደ ህገመንግስታዊ ፍርድ ቤት የመመለስ እድል የገጠመው ሲሆን እኤአ በማርች 23 ቀን 2023 በዋለው ችሎት ህገመንግስታዊ ፍርድ ቤቱ የኢምግሬሽን ደንብ አንቀፅ 63 ከህገመንግስቱ ጋር የሚጣረስ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን የኮሪያ ብሄራዊ ፖርላማውን የኢምግሬሽን ደንብ ማሻሻያ አድርጎ ከህገመንግስቱ ጋር የተጣጣመ መሆኑን እዲያረጋግጥ ሃላፊነት ሰቶታል::

በፖርላማ ተወካይ ፓርክ ጁ ሚን አርቃቂነት የቀረበው ማሻሻያ የሚደረግበት የኢምግሬሽን ደንብ : እንዲሻሻሉ ያሻቸዋል ተብሎ የቀረበው ረቃቅ እንደሚለው ከሀገር የማባረር ውሳኔ ሂደት መመዘኛዎች መሠረት የኢምግሬሽን እስር የመጨረሻው መጠባበቂያ መሆን እንዳለበት አሳስቧል:: ረቂቁ የእስርን ጊዜ ገደብ እንዲኖረው እና የመባረር ውሳኔ በተላለፈባቸው የውጭ ዜጎች ላይ የአስር አስፈላጊነት እና ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳት ከታሳሪው ሁኔታ ጋር እንዲነፃፀር መፈቀድ አለበት ብሏል:: እንደዚሁም የውጭ ዜጎች መታሰርን በመቃወም ለችሎት አቤት እንዲሉ ይፈቅዳል:: በዚህም ወሰረት ረቂቁ አሻሚ የሆነ እስርን ለመከላከል ዝቅተኛ የህግ ዋስትና እንዲኖርና: የመነሻው የእስር ጊዜ ከ 20 ቀናት በላይ መራዘም ካለበትም በፍርድ ቤት ታይቶ መሆን ይገባዋል ብሏል::

ህገ መንግስታዊ ችሎቱ ራሱ “ በማቆያ ማሰር ህገንግስታዊ አይደለም” ብሎ ቢወስንም : የኢምግሬሽ ደንብ አንቀፅ 63 ንሁስ አንቀፅ 1 እስከ እኤአ ግንቦት 31 ቀን 2025 ዓ.ም በጊዜዓዊነት ተፈፃሚ እንዲሆን የተወው ቢሆንም : የውጭ ዜጎችን አሻሚ በሆነ ሁኔታ ማሰር የቀጠለ ሆኗል:: በቅርብ ጊዜ የ 3 ዓመት ልጅ ከአዋቂ ወንዶች ጋር መስኮት በሌለው ክፍል ውስጥ ለ 19 ቀን ታስሮ ነበር:: እኛም በቅንነት የማሻሻያው ደንብ በፍጥነት እንዲፀድቅ እና ህገ መንግስታዊ ያልሆነው ማሰር እንዲያበቃ ተስፋ እናደርጋለን::